Drop files to upload.
Faithlife Corporation

ውጤታማ የሆኑ የስብከት መግቢያዎች፣ ማጠቃለያዎች፣ እና አያያዦችን መርሆዎች...

Sermon  •  Submitted
0 ratings
· 1 view
Notes & Transcripts

ውጤታማ የሆኑ የስብከት መግቢያዎች፣ ማጠቃለያዎች፣ እና አያያዦችን

መርሆዎች ማቅረብ

መግቢያዎች፣ ማጠቃለያዎች፣ እና አያያዦች

አስፈላጊ ግብአቶች

አንደ ወዳጄ በአንድ ወቅት ስብከቱን ለየት ባለ መንገድ ለአድማጮቹ ሲያስተላልፍ አደመጥኩት፡፡ ስብከቱን ሲጀምር እንዲህ አለ፡- ‹‹የምወዳቸው ሁለት ምርጥ ምግቦች የልጅነት ጊዜዬን የሚያስታውሱኝ እና በልጅነት እመገባቸው የነበሩ ምግቦች ናቸው፡፡ አክስቴ ቤሲ ከሆምጣጤ ጋር በተደባለቁ ቅጠላቅጠሎች የምትሰራው ምግብ እንዴት ያስደስተኝ እንደነበር መቼም ቢሆን ከትውሰታዬ አይጠፋም፡፡ ለማንም በማትናገረው አቀማመም በመታገዝ ከራስዋ ጓሮ ካፈራችው የፈረንጅ ዱባ ጋር ቀላቅላ የምትሰራውና ሲበሉት ኩርሽም ኩርሽም የሚለው ኮምጣጣ ምግብ የእርሷ ሙያ መለያ ነበር፡፡ ይህ ልዩ ምግቧ ጎምዛዛውን ቅጠላ ቅጠል ገና ማኘክ ሲጀመር እንደ ድንጋይ ወፍጮ ከሚያሰማው ታላቅ ድምጽ በተጨማሪ ቅጠሉ ምላስህ ላይ ከመድረሱ በፊት የከንፈሮችህን ጫፍ ነክቶ ከንፈሮችህን ካጨማደደ በኋላ፣ ከመራራው ቅጠል ጋር ልዩ በሆነ መንገድ የተዋሃደው ማጣፈጫ ከቅጠላ ቅጠሎቹ ጋር ተዋህዶ ምላስህ ላይ ሲያርፍና ልዩ ጣዕሙ በምላስህ ላይ ኮለል ሲል ድገሙኝ ድገሙኝ የሚል ልዩ ስሜት ይፈጥርብሃል፡፡ ይህ የቅጠላ ቅጠል ምግብ በአክስቴ ቤት መኖሪያ አካባቢ ባለው ቤተ ክርስቲያን የማደርገውን የበልግ ወራት ሽርሽር ልዩ የሚያደርግልኝ እንደነበር አስታውሳለው፡፡ ምግቡ በአክስቴ ቤት የማደርገውን ቆይታ በልዩ ሁኔታ ቢከፍትም በፍቅር የተሞላው የአክስቴ ቀጣይ መስተንግዶው ግን እየደመቀ ይሄዳል፡፡ ረፋድ ላይ በሚኖረው የስብከት ጊዜ ደግሞ ሚሲሲፒ ውስጥ በሚገኘው በገጠራማው የሬድ ባንክ አካባቢ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት አንድ የተለመደ ነገር ነበር፡፡ ሴቶች በግላጭ በሚነደው እሳት ላይ በተጣዱት የሻይ ጀበናዎች ዙሪያ ከበው ያወጋሉ፡፡ በእሳት ውስጥ በተጋደሙት ጉማጅ የዛፍ ግንዶች እና በመስክ በጥበሻው በሃከል ከሚትጎለጎለው ጭስ በሃል አንድ ልዩ ነገር እየሆነ ነው፡፡ ከልዩ ቅመም፣ ስኳር፣ ጣፋጭ ሊጥ እና ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎች የሚዘጋጀውን ኬክ ለመብላት ሁሉም በጉጉት ይጠባበቃል፡፡ የተጠበቀው ኬክ ደርሶ ሲበላ ምላስንም አብሮ መዋጥ እስኪያሰኝ ድረስ ልዩ ጣእም ይሰጥ እንደነበረ መቼም አልዘነጋውም፡፡ ካደግሁ በኋላ አክስቴ ቤሲ ቤት ይሰራ የነበረውን የቅጠላ ቅጠል ምግብ እና በሚሲሲፒ፣ ሬድ ባንክ ይጋገር የነበረውን ልዩ ጣእም ያለውን ኬክ ለማግኘት እግሬ ያልኳተነበት ስፍራ አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን ለዚህ ስብከቴ መግቢያ ለማግኘት እንዳልተሳካልኝ ሁሉ ምግቦቹንም ለማግኘት ያደረኩት ጥረት መና ሆኖ ቀርቷል፡ ››

ወዳጄ ይህን ታሪክ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ እርሱ -መግቢያ የሌለው- ወዳለው ስብከቱ ገባ፡፡ ሰባኪው ሆን ብሎ አድረጎት ይሆንም አይሆን፣ መግቢያ የሌለው ብሎ ባቀረበው ስብከቱ መነሻ ላይ ያቀረበው የልጅነት ጊዜው ትውስታ፣ የስብከቱ መግቢያ ነበር፡፡ በምናቀርበው መልዕክት ውስጥ መግቢያ፣ ማጠቃለያና ማያያዣ ሊቀሩ የማይችሉ ነገሮች ናቸው፡፡ መልዕክቱን የማቅረብ ፍላጎታችን እና የአቀራረብ ችሎታችን ምንም ይሁን ምን፣ እነዚህ ሶስት ነገሮች አይቀሬ ጉዳዩች ናቸው፡፡ መልዕክትህን የምትከፍትባቸው ቃላት የመልዕክትህ መግቢያ ሲሆኑ፤ የምትደመድምበት ቃላት ደግሞ የመልዕክትህ ማጠቃለያ ናቸው፤ እነዚህን ሁለት ክፍሎች አጣምረው የሚይዙ የመልዕክትህ ሌሎች ክፍሎች ደግሞ አያያዦች ይባላሉ፡፡ ዋናው ቁም ነገር፣ እነዚህ ሶስት የስብከትህ ክፍሎች በመልዕክትህ ውስጥ መኖር አለመኖራቸው ሳይሆን መልዕክትህን ለማስተላለፍ ጠቃሚ ሆነዋል ወይስ ደንቃራ የሚለው ነው፡፡ ይህን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ አስቀድሞ የሶስቱንም ክፍሎች አላማና ባሕሪያት ጠንቅቆ ማወቅ የግድ ይሆናል፡፡ ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የሚከተሉትን ዌብ ሳይቶች ይጎብኙ፡

http://islam-in-ethiopia.blogspot.com

http://decipling-believers.blogspot.com

http://teachings-of-orthodox-church.blogspot.com

http://bible-question-and-answer.blogspot.com

http://children-bible-lessons.blogspot.com/

RELATED MEDIA
See the rest →
Get this media plus thousands more when you start a free trial.
Get started for FREE
RELATED SERMONS
See the rest →