እምነትና ሃይማኖት በአዲስ ኪዳን

የክትትል ትምሕርት  •  Sermon  •  Submitted
0 ratings
· 256 views
Notes
Transcript
Sermon Tone Analysis
A
D
F
J
S
Emotion
A
C
T
Language
O
C
E
A
E
Social
View more →
ሐይማኖት የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የዋለባቸው ስፍራዎችና የሚያሳየውን ትርጉም እንመልከት
ሐዋርያት 6፥7 “የእግዚአብሔር ቃል እየሰፋ ሄደ ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቁጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ”
በዚህ ቃል ውስጥ የምንመለከተው ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት ሊታዘዙ የቻሉት የእግዚአብሔር ቃል እየሰፋ ከመምጣቱ የተነሳ እንደሆነ እናያለን። ለሃይማኖት መታዘዝ የምንችለው ለእግዚአብሔር ቃል ስንታዘዝ ብቻ እንደሆነ መረዳት እንችላለን። በዚህ መሰረት ለሃይማኖት መታዘዝ ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ እንደሆነ እናያለን
ሐዋ. 14፥21-22 “በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ”
ሐዋርያት እጅግ የሆኑ ደቀ መዛሙርትን ያፈሩት ወንጌልን ሰብከው ነው። ሐዋርያት የደቀ መዛሙርትን ልብ ያጸኑትና በሃይማኖት እንዲጸኑ የመከሩት የሰበኩላቸውን የወንጌልን እውነት መሠረትና ምክንያት በማድረግ ነው። በሃይማኖት መጽናት የሚቻለው በተሰበከልን የወንጌል እውነት በመጽናት ነው። ይህንን የምናደርገው የሰማነውን ቃል በልባችን በመጠበቅና ቃሉን በሚታዘዝ ሕይወት በመኖር ነው።
1ኛ ቆሮ. 16፥13 “ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ”
2ኛ ቆሮ. 13፥5 “በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን”
ገላ. 1፥23 “ቀድሞ እኛን ያሳድድ የነበረ፥ እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረውን ሃይማኖት አሁን ይሰብካል ተብሎ ሲነገር ይሰሙ ነበር”
ጳውሎስ የክርስትና ሃይማኖትን ሲያጠፋ የነበረው የክርስትናን እምነት የሚያምኑትንና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመሰክሩና ሲሰብኩ የነበሩትን አማኞች በማሳደድ ነበር። ጳውሎስ ክርስቲያኖችን በማሳደድ ያጠፋው የነበረውን ሃይማኖት አሁን ይሰብካል መባሉ ሃይማኖት በስብከት የሚተላለፍ እንደሆነ ያሳያል።
ገላ. 6፥10 “እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ”
የሃይማኖት ቤተ ሰቦች አንድ አይነት አምነት ያላቸውን ሰዎች የሚያሳይ ነው። እንዲህ ያለው ቤተ ሰብነት የሚገኘው ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ነው።
ኤፌ. 4፥5 “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት”
አንድ ሃይማኖት ማለት አንድ ቤተ እምነት ማለት አይደለም። አንድ ሃይማኖት ማለት አማኞች ሁሉ ሊያምኑት የሚገባው እምነት አንድ የሚያደርገው የምናምነው አንድ ጌታ ነው። አንዱን ጌታ ያመኑ በአንዱ ጌታ አንድ ሃይማኖት ይኖራቸዋል።
ፊል. 1፥27 “ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ”
ሃይማኖት ከወንጌል የሚገኝ ነው። ወንጌል የሃይማኖት ምንጭና ምክንያት ነው።
ቆላ. 1፥23 “ይህም፥ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ፥ በሃይማኖት ጸንታችሁ ብትኖሩ ይሆናል። ያም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፥ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ”
አማኞች በሃይማኖት ጸንተው የሚኖሩት ከሰሙት ወንጌል ተስፋ ሳይናወጡ የሚኖሩ ከሆነ ነው። የሰማነውን አጽንተን በመጠበቅ በወንጌል እውነት ላይ ተመሥርተንና ተደላድለን ብንቆም በሃይማኖት እንጸናለን።
ቆላ. 2፥7 “ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ”
1ኛ ጢሞ. 3፥9 “ነውረኛ ረብ የማይወዱ፥ በንጹሕ ሕሊና የሃይማኖትን ምሥጢር የሚይዙ ሊሆኑ ይገባቸዋል”
ሃይማኖት በውስጡ ብዙ ምሥጢራት አሉት። እነዚህ ምሥጢራት ከወንጌል የሚገኙ ናቸው። አማኞች እነዚህን ምሥጢራት በልባቸው በሚገባ ሊጠብቁ ይገባቸዋል።
1ኛ ጢሞ. 4፥1-2 “መንፈስ ግን በግልጥ። በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው”
ሰዎች ሃይማኖትን ሊክዱ ከሚችሉባቸው ክፉ ምክንያቶች መካከል አድኑ በመናፍስትና በውሸተኞች ግብዝነት የሚሰጠውን አጋንንታዊ ትምሕርት በማዳመጥ ነው። የሃይማኖትን እውነት መጠበቅ የምንችለው ከስህተት ትምሕርት ራሳችንን በመጠበቅ ነው።
1ኛ ጢሞ. 5፥8 “ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው”
1ኛ ጢሞ. 6፥10 “ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ”
2ኛ ጢሞ. 4፥7 “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ”
ሃይማኖት የሚጠበቀው የወንጌልን እውነት በመጠበቅ ነው።
ቲቶ 1፥4 “በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን”
ቲቶ 1፥13-14 “ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው”
ይሁዳ 1፥3 “ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ”

ከላይ ባየናቸው ጥቅሶች ሃይማኖት የሚለው ቃልና እምነት የሚለው ቃል ከአንድ ተመሳሳይ የግሪክ ቃል የተገኙ እንደሆኑ እንመለከታለን። ይህንን ለማየት የሚከተሉትን ጥቅሶች በማገንዘብ መረዳት ይቻላል።

ለሃይማኖት መታዘዝ ለእምነት መታዘዝ ነው
ሐዋርያት 6፥7 “የእግዚአብሔር ቃል እየሰፋ ሄደ ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቁጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ
ለሃይማኖት መታዘዝ የሚለው ቃል ሃይማኖት የሚለው የተተረጎመው “πίστει/ፒስቴይ” ከሚለው ቃል ነው።
ሮሜ 16፥25-26 “እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥ 27 ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን”
ለlእምነት የሚለው ቃል ለሃይማኖት መታዘዝ ሆኖ የተተረጎመው “πίστει/ፒስቴይ” ከሚለው ቃል ነው።
2ኛ ቆሮ. 13፥5 “በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን”
በሃይማኖት የሚለው ቃል በግሪክ “πίστει/ ፒስቴይ” የሚለውን የግሪክ ቃል ነው የሚጠቀመው።
ሮሜ 1፥17 “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና” ጻድቅ የሚኖርበት ሃይማኖት በግሪክ “πίστει/ፒስቴይ” የሚለውን ቃል ሲሆን ይህም ቃል እምነትም ሆነ ሃይማኖት ተብሎ እንደሚተረጎም እናያለን።
ገላ. 1፥23 “ያጠፋው የነበረውን ሃይማኖት አሁን ይሰብካል”
ሃይማኖት የሚለው ቃል የተተረጎመው በግሪክ “πίστιν/ፒስቲን” ከሚለው ቃል ነው።
ሮሜ 10.8 “የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው”
ጳውሎስም የሚንሰብከው የሚለው የእምነት ቃል በግሪክ “πίστεως/ ፒስቴዎስ” የሚለውን የግሪክ ቃል ነው የሚጠቀመው።
ኤፌ. 4፥5 “አንድ ሃይማኖት” ሃይማኖት የሚለው ቃል “πίστις/ፒስቲስ” የሚለው የግሪክ ቃል ነው።
ይሁዳ 1፥3 “ለቅዱሳን አንድ ግዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ “πίστει/ፒስቴስ” የሚለው የግሪክ ቃል ነው አማኞች የሚጋደሉለት ሃይማኖት።
ከላይ በሰንጠረዡ ላይ እንደ ተመለከትነው ሃይማኖትና እምነት ከአንድ የግሪክ ቃል የተተረጎሙ ቃላት በመሆናቸው ሃይማኖት ሌላ ትርጉም እምነት ደግሞ ሌላ ትርጉም ያለው እንደሆነ አድርገን መመልከት የለብንም። እምነት ሃይማኖት እንደ ሆነ ሃይማኖትም እምነት እንደ ሆነ ካወቅን የሃይማኖት ምንጩ ምን እንደ ሆነ መረዳት ደግሞ ተገቢ ነው።
ሃይማኖት እምነት እምነትም ሃይማኖት መሆኑን ተመለከትን። እምነት ምንድር ነው እንዴትስ ሊኖረን ይችላል?
እምነት ምንድር ነው?
ዕብ. 11፥1 “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። 2 ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። 3 ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን”
እምነት ተስፋ የምናደርገውን ነገር ይረጋገጥልና
የማናየውን ነገር እንረዳለን
ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ እናስተውላለን
የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳለሆነ በእምነት እንረዳለን
ተስፋ የምናደርገውን ነገር ከየት እናገኛለን? ስለማናየውን ነገር እምነት እንዴት ያስረዳናል?
የሃማኖት እውነት የሚገኝባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት
የሕግ መጻሕፍት
ዘፍጥረት
ዘፀዓት
ዘሌዋውያን
ዘሑልቅ
ዘዳግም
የታሪክ
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ
መጽሐፈ መሳፍንት
መጽሐፈ ሩት
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ
መጽሐፈ ዕዝራ
መጽሐፈ ነህምያ
መጽሐፈ አስቴር
የቅኔና የግጥም መጻሕፍት
መጽሐፈ እዮብ
መዝሙረ ዳዊት
መጽሐፈ ምሳሌ
መጽሐፈ መክብብ
መሐልየ መሐልይ ዘሰለሞን
አራቱ ዋና ነቢያት
ትንቢተ ኢሳይያስ
ትንቢተ ኤርምያስ
ሰቆቃወ ኤርምያስ
ትንቢተ ሕዝቅኤል
ትንቢተ ዳንኤል
12ቱ ነቢያት
ትንቢተ ሆሴዕ
ትንቢተ አሞጽ
ትንቢተ ሚክያስ
ትንቢተ ኢዩኤል
ትንቢተ አብድዩ
ትንቢተ ዮናስ
ትንቢተ ናሆም
ትንቢተ እንባቆም
ትንቢተ ሶፎንያስ
ትንቢተ ሐጌ
ትንቢተ ዘካርያስ
ትንቢተ ሚልክያስ
ሃያ ሰባቱ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት
ወንጌላት
ማቴዎስ
ማርቆስ
ሉቃስ
ዮሐንስ
የመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ
የሐዋርያት ስራ
የጳውሎስ መልእክቶች
ወደ ሮሜ ሰዎች
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1ኛ
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2ኛ
ወደ ገላትያ ሰዎች
ወደ ኤፌሶን ሰዎች
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
ወደ ቆላስይስ ሰዎች
ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 1ኛ
ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2ኛ
ወደ ጢሞቴዎስ 1ኛ
ወደ ጢሞቴዎስ 2ኛ
ወደ ቲቶ
ወደ ፊልሞና
ወደ ዕብራውያን
አጠቃላይ መልእክቶች
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት
2ኛ የጴጥሮስ መልእክት
1ኛ የዮሐንስ መልእክት
2ኛ የዮሐንስ መልእክት
3ኛ የዮሐንስ መልእክት
የያዕቆብ መልእክት
ይሁዳ
የትንቢት መጽሐፍ
ራዕይ